እንኳን ለ2017 የከተራና የጥምቀት በዓል አደረሳችሁ።
Happy Ketera and Epiphany celebration! Join us on our updated platform: https://p2pbridge.org
እንኳን ለ2017 የከተራና የጥምቀት በዓል አደረሳችሁ። Read More »
Happy Ketera and Epiphany celebration! Join us on our updated platform: https://p2pbridge.org
እንኳን ለ2017 የከተራና የጥምቀት በዓል አደረሳችሁ። Read More »
P2P celebrated Christmas with joy and giving! Ms. Alexia and her two sons shared gifts with children, and Dr. Zewedu, P2P’s Country Representative, inspired us with a heartfelt speech on unity. Thank you to everyone who joined us in spreading smiles and building stronger communities! #P2PChristmas#TogetherWeGrow#CommunityMatters
P2P Celebrates Christmas with Joy and Giving! Read More »
P2P Christmas Celebration with Love and Joy January 11, 2025 | Addis Ababa, Ethiopia
Join us on our updated platform: https://p2pbridge.org
እንኳን ለብርሃነ ልደቱ አደረሳችሁ! Happy Ethiopian Christmas from P2P! Read More »
We are thrilled to announce the news coverage of an exclusive interview with Dr. Enawgaw Mehari, founder and president of People to People (P2P), featured in The Reporter Magazine. This piece highlights P2P’s impactful contributions to healthcare, education, and development in Ethiopia and beyond. Read the full article here: https://www.ethiopianreporter.com/136692/ Stay connected and explore our updated platform: https://p2pbridge.org የፒፕል ቱ ፒፕል አበርክቶ ካለፉት 25 ዓመታት ወዲህ በሦስትዮሽ አጋርነት ትብብር በኢትዮጵያ በተለይ የጤናውን ዘርፍ ለማጠናከር እየሰራ የሚገኘው ፒፕል ቱ ፒፕል (ፒቱፒ) ለመመሥረቱ ምክንያት የሆነው፣ በወቅቱ ኤችአይቪ ኤድስ የኢትዮጵያ ትልቁ የጤና ችግር ስለነበር ነው፡፡ ኤችአይቪ ኤድስ ለዓለም የጤናው ዘርፍና ለጤና ባለሙያውም ቢሆን ፈተና ነበር፡፡ ለደሃ አገሮች ደግሞ ከባድ ቀውስ ያስከተለ ነው፡፡ ኢትዮጵያም በርካታ ልጆቿን በቫይረሱ አጥታለች፡፡ ችግሩን በጋራ ሆኖ ለመቅረፍ በማለም በአሜሪካ የተቋቋመው ድርጅቱ፣ እናትና አባታቸውን በኤድስ ያጡትን በመመገብ፣ በማስተማርና ግንዛቤ በመፍጠር ሲሠራ ቆይቶ በሒደት ፒቱፒ ካናዳ፣ ፒቱፒ ስዊድን፣ ፒቱፒ ፊንላንድ፣ ፒቱፒ ስዊዘርላንድ አቋቋመ፡፡ የፒቱፒ የኢትዮጵያ ፕሮግራሞች ማስተባበሪያም በአዲስ አበባ ተከፈተ። ፒቱፒ በኢትዮጵያና በውጭ በሚኖሩ ኢትዮጵያውያን መካከል የጤና እንክብካቤን፣ ልማትንና ትምህርትን ለማሻሻል የተመሠረተ ለትርፍ ያልተቋቋመ ድርጅት ሲሆን፣ ዳያስፖራውን መሠረት አድርጎ፣ በተቋማት መካከል ድልድይ ለመፍጠር በዓለም አቀፍ ደረጃ በሚገኙ ዳያስፖራዎች መካከል ግንኙነትን የሚፈጥርና የሚያጠናክር የሦስት ማዕዘን አጋርነት የተሰኘ ፍልስፍና አለው፡፡ በኢትዮጵያ ከጤና ሚኒስቴር፣ ከትምህርት ሚኒስቴርና ከኢትዮጵያ ዩኒቨርሲቲዎች ጋር በተለያዩ መስኮች በመሥራትም 25 ዓመታትን አብሮ ዘልቋል፡፡ እናውጋው መሐሪ (ዶ/ር) የድርጅቱ መስራችና ፕሬዚዳንት ናቸው፡፡ ድርጅቱ ካበረከታቸው አንኳር በሆኑት ዙሪያ ምሕረት ሞገስ አነጋግራቸዋለች፡፡ ሪፖርተር፡- የኤድስ ሥርጭት ቢቀንስም መልሶ የማገርሸት ሁኔታ አለ፡፡ ሥራውን ቀጥላችሁበታል? እናውጋው (ዶ/ር)፡- ሥራውን ስንጀምር በኢትዮጵያ አንድም መድኃኒት አልነበረም፡፡ በወቅቱ መድኃኒቱ በኢትዮጵያ ስላልተመዘገበ ለማስገባትም ችግር ነበር፡፡ በመሆኑም መጀመርያ በማስተማር ጎን ለጎን ደግሞ መድኃኒት እንዲገባ ለማድረግ ተሠርቷል፡፡ የተለያዩ ድርጅቶች ጥረት ተጨምሮበት መድኃኒቱ ወደ ኢትዮጵያ በነፃ እንዲገባ በማድረግ የበርካቶችን ሕይወት ታድገናል፡፡ ኤችአይቪ ኤድስም እንደ ስኳር፣ ደም ግፊትና ሌሎችም በሽታዎች መቆጠር ጀመረ፡፡ ሞት ቀነሰ፡፡ እኛም ወደ ሌሎች ሥራዎች ላይ ማተኮር ጀመርን፡፡ እንደተባለው የማገርሸት ነገር ሊኖር ይችላል፡፡ በእኛ በኩል በደብረ ማርቆስ በአማኑኤል አዳሪ ትምህርት ቤት ለሚማሩ ተማሪዎች ስለቫይረሱ እናስተምራለን፡፡ ሪፖርተር፡- ከኤድስ በተጨማሪ በኢትዮጵያ በጣት የሚቆጠሩ ኒውሮሎጂስቶች በነበሩበት ወቅት የባለሙያዎችን ቁጥር ለመጨመር ሥልጠና ትሰጡ ነበር፡፡ ከምን ደረሰ? እናውጋው (ዶ/ር)፡- በወቅቱ በሙያው የሠለጠኑ ጥቂት ኒውሮሎጂስቶች ብቻ ነበሩ፡፡ በመሆኑም በአሜሪካ የተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎችን አቀናጅተንና ተማሪዎች መልምለን በኢትዮጵያ የመጀመርያ ባች እንዲመረቅ አድርገናል፡፡ አሁን ላይ ራሱን ችሎ ፋኩልቲ ሆኗል፡፡ ሪፖርተር፡- የኢመርጀንሲ ሜድስን በሕክምና ትምህርት እንደ ዲፓርትመንት እንዲካተት ጥረት አድርጋችሁ ተሳክቷል፡፡ አሁን እንዴት ትገመግሙታላችሁ? እናውጋው (ዶ/ር)፡- በኢትዮጵያ የሕክምና ታሪክ የኢመርጀንሲ ትምህርት በሕክምና ትምህርት ውስጥ ይሰጥ ነበር፡፡ ፒፕል ቱ ፒፕል ከአሜሪካ ጤና ኢንስቲትዩት፣ ከዊስኮንሲን ዩኒቨርሲቲና ከጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ጋር በመተባበር የኢትዮጵያ ሐኪሞች በኢመርጀንሲ ሜድስን ስፔሻላይዝ እንዲያደርጉ ሥልጠና ጀምረን የመጀመርያ ባች ከዓመታት በፊት አስመርቀናል፡፡ ስፔሻላይዜሽኑ በሌሎች ዩኒቨርሲቲዎችም ተጀምሯል፡፡ ውጤታማም ሆነናል፡፡ በተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች ያሉ የኢመርጀንሲ ዲፓርትመንቶችም በሠለጠነ ባለሙያ እየተመሩ ነው፡፡ የፒቱፒ አሠራር ለመጀመርያ ጊዜ በማሳየትና በማሠልጠን ተቋማት ቀጣዩን በራሳቸው እንዲወጡት ማድረግ ነው፡፡ ሪፖርተር፡- ባለፉት 25 ዓመታት ትኩረታችሁ ተቋማትን ማጠናከርና ክፍተቶችን መሙላት ላይ ነበር፡፡ ሆኖም የካንሰር፣ የጉበት፣ የኩላሊትና ሌሎችም ተላላፊ ያልሆኑና የተራቀቀ ህክምና የሚፈልጉ በሽታዎችን በአገር ውስጥ መታከም የኢትዮጵያውያን ፈተና ነው፡፡ በ25 ዓመታት የሕክምና ድጋፍ ጉዟችሁ ለምን እነዚህን የሚያክም ሆስፒታል አላቋቋማችሁም? እናውጋው (ዶ/ር)፡- ሆስፒታል ለማቋቅም ለረዥም ጊዜ ሙከራ ሲደረግ ነበር፡፡ ከ150 በሚልቁና በሰሜን አሜሪካ በሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ዶክተሮች ኢትዮ-አሜሪካ የዶክተሮች ቡድን ተቋቁሞ ከመንግሥት ጋር ሆነው ለመሥራት ተሞክሮ አልተሳካም፡፡ ከፒቱፒ በላይ አቅም ያላቸው ዶክተሮች ናቸው ሥራውን ለመጀመር ሲንቀሳቀሱ የነበሩት፣ መሬት ተሰጥቷቸውም ነበር፡፡ ሆኖም በተለያዩ ችግሮች ምከንያት ዕውን ሊሆን አልቻለም፡፡ ልክ ኒውሮሎጂና ኢመርጀንሲ ትምህርት ክፍል እንዲጀመር እንዳደረግነው ባይሆንም፣ በካንሰር ሕክምናና ስፔሻላይዜሽን በኩል ያለውን ክፍተት ለመሙላት የሰው ኃይል ማሠልጠን ስለሚገባ ከሜዮ ክሊኒክ ጋር በመሆን በመስከረም 2017 ዓ.ም. ፊሎውሺፕ ተጀምሯል፡፡ የጉበት በሽታን በተመለከተ ካሊፎርኒያ ያለችው ቅድስት ኪዳኔ (ዶ/ር) ጥረት እያደረገች ነው፡፡ በሰሜን ካሊፎርኒያ ያሉ ባልደረቦቿን በማስተባበር በቅዱስ ጳውሎስ ሚሊኒየም ሜዲካል ኮሌጅ የጉበት ንቅለ ተከላን ጨምሮ የተለያዩ አገልግሎቶች መስጠት የሚያስችል የህክምና ክፍል ለመመስረት በመስራት ላይ ነች። ነገር ግን እነዚህን ጥረቶች መንግሥት እኔም ይመለከተኛል ብሎ ቅድሚያ ሰጥቶ አብሮ መሥራት ካልቻለ መቀጠል አይቻልም፡፡ መድኃኒት ማስገባት በራሱ ከባድ ነው፡፡ በዳያስፖራው በኩል በጤናው ዘርፍ ትልቅ ለውጥ ለማምጣት ብዙ ሙከራዎች ተደርገዋል፡፡ በእኛ በኩል በኢትዮጵያ ፕራይድ የሚባል ሆስፒታል ለማቋቋም አቅደን ሥርዓቱ ግን የሚያሠራን አልሆነም፡፡ አንድ አገር ለመሠልጠን ጥሩ ትምህርትና ጥሩ የጤና ሥርዓት ያስፈልገዋል፡፡ ለዚህ ደግሞ ቅድሚያ ሰጥቶ መሥራትን ይጠይቃል፡፡ ዛሬ ላይ ከዓለም ዕውቅ የሆኑ የሕክምና ባለሙያዎች ታይላንድ ውስጥ እንዲሠሩ ያስቻለው የተመቻቸ አሠራር ስለተዘረጋ ነው፡፡ ኢትዮጵያም ሊያሰራ የሚችል ሥርአት መተግበር አለባት፡፡
P2P Contribution: Reporter Magazine Features Dr. Enawgaw Read More »
This festive season, we at People to People (P2P) extend our heartfelt gratitude to our incredible community of supporters, partners, and volunteers. Together, we’ve made a lasting impact on healthcare, education, and development. 🌍💙 As we celebrate the joy of Christmas and welcome a new year filled with hope and possibilities, let’s continue to build bridges and transform lives. 🌟 Wishing you and your loved ones a season full of peace, love, and happiness! 🌟 Join us on our updated platform: https://p2pbridge.org #MerryChristmas #HappyNewYear #P2PGlobal #TransformingLives #CommunityMatters #2025
🎄✨ Merry Christmas and Happy New Year! ✨🎄 Read More »
ዶ/ር አብርሃም በትረ የፒፕል ቱ ፒፕል የሥራ ኃላፊ፣ ዶ/ር እናውጋው መሃሪ የፒፕል ቱ ፒፕል መስራች ፕሬዝዳንት P2P 25th Anniversary VoA Media Coverage
በሕክምና የበጎ አድራጎት አገልግሎቶች የሃያ አምስት ዓመታት ጉዞ Read More »
🎥 Watch the Highlights: https://youtu.be/a5k40vi53KA🌐 Learn more: www.p2pbridge.org #P2P25Years, #AIAfrica, #BuildingBridges
🎉 P2P 16th Annual Conference & 25th Anniversary Highlights Read More »
On October 19, 2024, People to People (P2P) proudly celebrated a quarter-century of transformative impact at its 16th Annual Conference held in the USA. 🎥 Watch the Conference Highlights: https://www.youtube.com/watch?v=CHlTM96K4z4 ✨ Visit our newly updated platform for more updates: www.p2pbridge.org